አላህን (سبحانه و تعالى) በአምልኮትና እርሱ ከፍጥረታቱ በሚለይበት ባህሪያት አንድ ማድረግ እና መነጠል ተውሒድ ሲባል፤ በእያንዳንዱ አማኝ ማመኑ ግዴታ የሆኑ ነገሮች እና ከህዋስ የራቁ ነገሮች ማመን ዐቂዳ ይባላል።
ለምሳሌ፦ በአላህ ማመን ፣ በመላክት መላክ ፣ በመጽሃፍት መውረድ ፣ በመልክተኞች መላክ፣ በመጨረሻ ቀን ሞቶ መቀስቀስ፣ በአላህ ውሳኔ ማመን እና ሌሎች ከዚህ ጋር የተያያዙ ነጥቦችን ማመን ዐቂዳ ይባላል።
አላህ እውቀትን ለሌሎች የማካፈልን ትሩፋት ሲናገር እንዲህ ይላል፦
"ومن أحسن قولا ممن دعا إلى الله وعمل صالحا وقال إنني من المسلمين"
“ወደ አላህ ከተጣራና መልካምንም ከሰራ፣ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?”
ነቢያችንም(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል “እውቀትን ፍለጋ መንገድን የተጓዘ አላህ የጀነትን መንገድ ያመቻችለታል።” (ሙስሊም ዘግበውታል 2699)
የሐዲሥ ት\ት ዓላማዎች፦
ለአለህ ምስጋና ይገባው። የአላህ ሰላምና እዝነት በነብያችንና በወዳጃችን በአለህ መልዕክተኛ ላይ ይሆን።
በመቀጠልም ነቢዩ ሙሀመድ (×) እንዲህ ይላሉ፦
> خيركم من تعلم القرآن وعلمه <
ከሁላችሁም የሚበልጠው ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።(ቡኻሪ ዘግበውታል)
የአረብኛ ፊደላት መውጫ ቦታዎች በጥቅሉ 5 ሲሆኑ እነሱም፦
1- ጀውፍ
2- ጉሮሮ
3- ምላስ
4- ከንፈሮች
5- ኮሽኮሽ( አፍንጫ )ናቸው።